ዓለምአቀፋዊ ዜና

በጥቁር ባሕር ጉዳይ የአሜሪካንም ሆነ የ“ኔቶ”ን ጣልቃ-ገብነት እንደማትሻ ቱርክ አስታወቀች

By Alemayehu Geremew

November 19, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጥቁር ባሕር ጉዳይ ላይ የአሜሪካንም ሆነ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ)ን ጣልቃ-ገብነት እንደማትሻ ቱርክ አስታወቀች፡፡

በቀጣናው የደኅንነት ጉዳይ ላይ እራሷ ቱርክ እንደምትበቃም የሀገሪቱ ባሕር ኃይል ጦር አዛዥ ኤጁመንት ታትሎውሎ ተናግረዋል፡፡

በጣልቃ-ገብ ኃይሎች ቀጣናው እንዲረበሽ እንደማይፈልጉ በአጽንኦት መግለጻቸውንም መኽር ዘግቧል፡፡

በአውሮፓ እና እሲያ መካከል የሚገኘውን ጥቁር ባሕር ÷ ዩክሬን፣ ሩሲያ፣ ጆርጂያ፣ ቱርክ፣ ቡልጋሪያ እና ሮማኒያ በጋራ ይጠቀሙበታል፡፡