አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በቀን ሁለት ቦቴ ነዳጅ ወደ ጋዛ ሰርጥ እንዲገባ እንደምትፈቅድ ገልፃለች።
እስራኤል እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በአሜሪካ በኩል ግፊት ስለበዛባት እንደሆነም ተመላክቷል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣን እንደተናገሩት በየሁለት ቀኑ 140 ሺህ ሊትር ነዳጅ ወደ ጋዛ እንዲገባ ይፈቀዳል።
ከሚገባው ነዳጅ ውስጥ አብዛኛው ሰብአዊ እርዳታ ለሚያቀርቡ እና ተመድ በስፍራው ለሚያደርሰው የመጠጥ ውሃ እና የንፅህና መጠበቂያ አቅርቦት ለሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎች መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል።
ቀሪው በነዳጅ እጦት ተቋርጦ የነበረው የሞባይል እና የኢንተርኔት አገልግሎት ለማስቀጠል የሚውል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በትናንትናው ዕለት ለጋዛ የኢንተርኔት አቅራቢ የሆነው ድርጅት በተመድ የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ በኩል የተወሰነ ነዳጅ ማግኘቱን ተከትሎ አገልግሎቱ እየጀመረ መሆኑን አስታውቋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!