Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጋዛ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ምግብና ሌሎች ድጋፎችን ማድረስ እንዳልተቻለ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት የተነሳ በጋዛ የግንኙነት መሥመር ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ምግብና ሌሎች የሰብዓዊ አቅርቦቶችን ወደ ሥፍራው ማድረስ እንዳልቻሉ ዓለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች ተናገሩ፡፡

ድርጅቶቹ የሚሠጡትን አገልግሎት በዛሬው ዕለት ሙሉ በሙሉ ማቋረጣቸውን ተከትሎ ንጹሐን ሊራቡ እንደሚችሉ ማስጠንቀቃቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

የበይነ-መረብ እና የሥልክ አገልግሎት የተቋረጠው ወደ ጋዛ ይደርስ የነበረው ነዳጅ መቆሙን ተከትሎ ነው፡፡

አሁን ላይ የግንኙነት መሥመሮች መቋረጣቸውን ተከትሎ 2 ነጥብ 3 ሚሊየን የሚደርሰው በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የሚኖረው የጋዛ ሕዝብ ለመገናኘት መቸገሩ ነው የተገለጸው፡፡

በሌላ በኩል የእስራዔል ጦር በሰሜናዊው የጋዛ ክፍል እያካሄደ ያለውን ጥቃት ወደ ደቡብም ማስፋት እንደሚፈልግ ምልክት አሳይቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version