አዲስ አበባ፣ ኅዳር 7 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኮሪያው ግዙፉ የሳምሰንግ ኩባንያ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ጄይ ሊ በአክሲዮን ማጭበርበርና በሒሳብ አያያዝ ችግር ክሥ ተመሠረተባቸው።
የደቡብ ኮሪያ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት÷ የሳምሰንግ ኤሌክትሮኒክስ ኃላፊ ጄይ ሊ በፈረንጆቹ 2015 የኩባንያው አጋሮች አክሲዮን እና ሒሳብ ላይ ለፈጸሙት የማጭበርበር ወንጀል በ5 ዓመታት እሥራት እንዲቀጡ ጠይቋል።
ከፍተኛ የአክሲዮን ምዝበራ እንደተፈጸመ እና ሒሣብ ላይም ማጭበርበር መኖሩን ዐቃቤ ሕግ መግለዑን ዘ ኒውስ ዴይሊ አስነብቧል፡፡
የኩባንያው ዋና ሥራ አሥፈፃሚ በምላሻቸው ምንም ዓይነት ስህተት አልሠራሁም ብለዋል።
የግዙፉን ኩባንያ ኃላፊ ላይ ክስ የመሰረተው ዐቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው ÷ የ 55 ዓመቱ ሊ እና የቀድሞ የሳምሰንግ ሥራ አሥፈፃሚዎች የካፒታል ገበያ ሕጉን ጥሰው እንደ “ሲ ኤንድ ቲ” እና “ቻይል ኢንዱስትሪስ” ባሉ አጋሮቻቸው ላይ የ8 ቢሊየን ዶላር የአክሲዮን ማጭበርበር ፈፅመዋል፡፡
በአንፃሩም ሳምሰንግ የኤሌክትሮኒክስ ገበያውን በበላይነት እንዲቆጣጠር ረድቶቷል።
ለሦስት ዓመታት የዘለቀው የፍርድ ሂደት በወራት ጊዜ ውስጥ ችሎቱ በመጨረሻ በሚሠጠው ብይን ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!