አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2016 (ኤ ፍ ቢ ሲ) የፀሐይ ኃይል በታዳጊ ሀገራት የጤና አገልግሎትን አስተማማኝ ለማድረግና ህይወትን ለመታደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ሲሉ ባለሙያዎች ተናገሩ፡፡
በታዳጊ ሀገራት የሚገኙ ሁሉም የጤና ተቋማት በአምስት ዓመታት ውስጥ ከ 5 ቢሊየን ዶላር ባነሰ ወጪ የፀሐይ ኃይልን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ኃይል ሊያገኙ ይችላሉ ሲሉ ባለሙያዎች በCop28 የመከራከሪያ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
በተያዘው ወር በሚካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የመከራከሪያ ሀሳብ ያቀረቡት ባለሙያዎቹ አገልግሎቱ በኤሌክትሪክ መቆራረጥ ምክንያት በህይወት ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለማስወገድ እንደሚረዳ አመላክተዋል፡፡
በዓለም ጤና ድርጅት የዘላቂ ኃይል አማካሪ እና የ Cop28 ልዑካን አባል ሳልቫቶሬ ቪንቺ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ “ሁሉንም የጤና ተቋማት የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ ቀነ-ገደብ እንዲያበጅ እና የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ እፈልጋለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።
አሁን ላይ ከ10 ዓመት በፊት ያልነበሩ መፍትሄዎች አሉን ያሉት ቪንቺ፤ ዛሬ ኤሌክትሪክ ስለሌለ ማሞቂያቸው ባለመንቀሳቀሱ ህጻናት የሚሞቱበት ምንም ምክንያት የለም ሲሉም ነው የገለጹት።
አያይዘውም ይህ ዝቅ ብሎ እንደተንጠለጠለ ፍሬ ነው እውን ከማድረግ የሚያግደን ነገር አይኖርም ብለዋል።
በዓለም ጤና ድርጅት ጤናን በኃይል መሙላት፣ የኤሌትሪክ ተደራሽነትን ማፋጠን በሚል በቪንቺ በተፃፈው እና በፈረንጆቹ ጥር ወር እንደታተመው ሪፖርት÷ በዓለም ዙሪያ ወደ 1 ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በጤና ተቋማት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ያለው እንክብካቤ አያገኙም፡፡
አሃዙ 433 ሚሊየን የሚሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ምንም ዓይነት የኤሌክትሪክ ንክኪ በሌላቸው መገልገያዎች ላይ ጥገኛ የሆኑ ተቋማትንም እንደሚጨምር መገለፁን ዘጋርዲያን ዘግቧል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!