የሀገር ውስጥ ዜና

አየር መንገዱ 16 አውሮፕላኖችን ለካርጎ አገልግሎት መድቦ እየሰራ መሆኑን ገለጸ

By Amele Demsew

November 16, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ ደንበኞች ቀንን በዛሬው ዕለት አክብሯል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው÷ አየር መንገዱ አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የካርጎ አየር መንገድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይም 16 አውሮፕላኖችን በማሰማራት አስተማማኝ የካርጎ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

አየር መንገዱ ባለፈው ዓመት 740 ሺህ ቶን የካርጎ ጭነት አገልግሎት መስጠት መቻሉን ጠቁመው÷ ለዚህም ደንበኞች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል ።

በመርሐ- ግብሩ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ተገኝተዋል።

በበረከት ተካልኝ