አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ትብብር አጠናክራ መቀጠል እንደምትፈልግ ገልጻለች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከሩሲያ አምባሳር ይቬጀኒ ተርኺኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በሩሲያ እና ኢትዮጵያ መካከል ባለው የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን ትብብር እንዲሁም በመጪው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ላይ መክረዋል፡፡
አምባሳደር ምስጋኑ ÷የሩሲያ መንግስት ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያከናወነች ባለው ተስፋ ሰጪ የግብርና ስራ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
አምባሳደር ኢቭጄኒ ተርኺኒ በበከሉቸው÷ ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን የጋራ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ ናት ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡