የሀገር ውስጥ ዜና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወርቅ አምራች ማህበራት ምርታቸውን በአግባቡ ወደ ብሔራዊ ባንክ እንዲያስገቡ ተጠየቀ

By Amele Demsew

November 16, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በወርቅ አምራች ማህበራት ምርቱን በአግባቡ ወደ ብሔራዊ ባንክ በማስገባት የሀገር ኢኮኖሚ የማሳለጥ ሚናቸውን እንዲወጡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን አሳሰቡ፡፡

በአቶ አሻድሊ ሀሰን የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በክልሉ የሚገኙ ወርቅ ማምረቻ ቦታዎችን እየጎበኘ ነው።

ርዕሰ-መስተዳድሩ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት፦ በወርቅ ምርት ላይ የተሰማሩ ማህበራት ምርቱን በአግባቡ ወደ ብሔራዊ ባንክ በማስገባት የክልሉን ብሎም የሀገርን ኢኮኖሚ የማሳለጥ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡

የማዕድን ሀብት እንደ ሀገር ከግብርናው ዘርፍ ቀጥሎ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት የጀርባ አጥንት መሆኑን ማስገንዘባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።