Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዘመናዊ የነዳጅ አሥተዳደር ሥርዓት ሥራ ላይ ሊውል ነው – ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ነዳጅ ለትክክለኛ ዓላማ እንዲውል የሚያደርግ ዘመናዊ የነዳጅ አሥተዳደር ሥርዓት ሥራ ላይ ሊውል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ ገለጹ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልሎች፣ ከከተሞች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርት ላይ በድሬዳዋ መክሯል።

በመድረኩም ኢትዮጵያ ነዳጅ ከውጭ ለማስገባት በየዓመቱ 4 ቢሊየን ዶላር እንደምታወጣ የገለጹት አቶ ገብረመስቀል ÷ ሐብቱን ከጥቁር ገበያ ንክኪ ነጻ ለማድረግ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም በአዲስ አበባና በሸገር ከተሞች በሙከራ ደረጃ የተተገበረው ዘመናዊ የነዳጅ አሥተዳደር ሥርዓት በቅርቡ በመላው ሀገሪቱ ተግባራዊ ይሆናል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከሰኔ 30 ቀን 2015 ጀምሮ በጅምላ ድጎማ ውስጥ የነበሩና ድጎማውን በአግባቡ ያልተጠቀሙ 1 ሚሊየን ተሽከርካሪዎችን ከድጎማ ሥርዓት በማውጣት በገበያ ዋጋ እንዲገዙ ማድረግ መቻሉንም ነው የገለጹት፡፡

ሥርዓቱ በመላ ሀገሪቱ ተወዳዳሪና ፍትሐዊ የንግድ ሥርዓት ለመገንባት የተጀመረውን የልማት ጉዞ ያግዛል ነው ያሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version