Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 11 ኤ350-900 አውሮፕላኖችን ለማዘዝ ከኤር ባስ ጋር ሥምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ 11 ኤ350-900 አውሮፕላኖችን ለማዘዝ የሚያስችል የመግባቢያ ሥምምነት ከአውሮፕላን አምራቹ ኤርባስ ጋር ተፈራረመ፡፡

ሥምምነቱ ተጨማሪ ስድስት አውሮፕላኖችን የመግዛት አማራጭን በውስጡ ያካተተ እንደሆነ ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት በ20 ኤ350-900 ኤር ባስ አውሮፕላኖች ስራ ላይ የሚገኙ ሲሆን ፥ ይህም የአፍሪካ ትልቁ የኤ350 ደንበኛ መሆኑን እንደሚያረጋግጥ ነው የተገለጸው።

ሥምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እና የኤር ባስ ዋና የንግድ ባለሙያ እና ኃላፊ ክርስቲያን ሼረር በተገኙበት ተፈርሟል።

አቶ መስፍን ጣሰው በዚህ ወቅት እንዳሉት ለክቡራን ደንበኞቻችን ምቹ እና የማይረሳ በቴክኖሎጂ የላቁ አውሮፕላኖችን በማቅረብ የበረራ አድማሳችንን ማስፋት እንፈልጋለን ብለዋል።

የኤርባስ ዋና የንግድ ባለሙያ እና ኃላፊ ክሪስቲያን ሼርር በበኩላቸው ፥ “የኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዩ የሆነውን ኤ350ን አውሮፕላን ለረጅም ርቀት ጉዞ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ትልቅ ምሳሌ መሆኑን ጠቅሰዋል ።

ኤ350 ኤር ባስ አውሮፕላን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ ሰፊ ሰው ጫኝ እና ከ300 እስከ 410 መቀመጫዎች ያለው የረጅም ርቀት አውሮፕላን ነው ተብሏል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version