ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና እና አሜሪካ የዓየር ንብረት ለውጥ ቀውስን ለመፍታት በትብብር ሊሠሩ ነው

By Alemayehu Geremew

November 15, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና እና አሜሪካ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን የዓየር ንብረት ለውጥ ቀውስ በትብብር ለመፍታት እንደሚሠሩ ገለጹ፡፡

ሀገራቱ ትብብራቸውን ለማሳደግ መስማማታቸውንና የጋራ መግለጫ ማውጣታቸውን የቻይና የሥነ-ምኅዳር እና የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ይፋ ማድረጉን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።

የቻይና የዓየር ንብረት ለውጥ ልዩ መልዕክተኛ ዢ ዠንዋ እና የአሜሪካ አቻቸው ጆን ኬሪ ከፈረንጆቹ ሐምሌ 16 እስከ 19 በቻይናዋ ቤጂንግ እንዲሁም ከኅዳር 4 እስከ 7 በአሜሪካ ካሊፎርኒያ መምከራቸው የሚታወስ ነው።

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ትናንት ተጀምሮ እስከ ፈረንጆቹ ኅዳር 17 በሚቆየው 30ኛው የእሲያ ፓስፊክ ሀገራት የምጣኔ – ሐብት ትብብር የመሪዎች ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ በዛሬው ዕለት አሜሪካ መግባታቸውም ነው የተመላከተው፡፡