የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰአታት ለ3 ሺህ 645 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 30 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

By Tibebu Kebede

May 22, 2020

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ3 ሺህ 645 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 30 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ 26 ወንድ እና 4 ሴቶች ናቸው።

ሁሉም ኢትዮጵያውያን ዜጎች ሲሆኑ ከ15 እስከ 60 አመት የሚገኙ ናቸው ተብሏል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል 18 አዲስ አበባ፣ 3 አፋር ክልል፣ 4 ኦሮሚያ ክልል፣ 3 ትግራይ ክልል እንዲሁም 2 የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ናቸው።

ከእነዚህ ውስጥ 9ኙ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ፥ 17 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው መሆኑ ተገልጿል።

አራቱ ደግሞ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ግንኙነት የሌላቸው ናቸው።

5 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አዲስ ያገገሙ ሲሆን ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 128 ደርሷል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።