Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኔፓል ቲክቶክን ልታግድ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኔፓል በህብረተሰቡ ማኅበራዊ መሥተጋብር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ያለችውን ‘ቲክቶክ’ የማህበራዊ ትሥሥር ገፅ አማራጭ ልታግድ መሆኗ ተሰማ፡፡

እንደ ገልፍ ቱዴይ ዘገባ፤ ኔፓል የቻይናውን ታዋቂ የማኅበራዊ ትሥሥር ገፅ በይፋ ልታግድ መሆኗን ያስታወቀችው ዛሬ ነው፡፡

የማኅበራዊ ትሥሥር ገጹን ለማገድ የተገደደችው÷ በቲክቶክ በሚለቀቁት ተንቀሳቃሽ ምሥሎች የሚተላለፉት መልዕክቶች ለሀገሬው ሰው ባሕል እንግዳ የሆኑ እና ቀድሞ በሕብረተሰቡ ዘንድ የነበረውን ማኅበራዊ መሥተጋብር በመሸርሸራቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

እንደ ኔፓል መገናኛ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሬካ ሻርማ÷ ጉዳዩ አሳሳቢ በመሆኑ የሀገሪቷ ካቢኔ ተሰብስቦ እንደመከረና ለማገድ ውሳኔ እንዳሳለፈ ጠቁመዋል፡፡

የኔፓል ቴሌኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ኃላፊ ፑሩሾታም ካናል በበኩላቸው÷ በኔፓል የሚገኙ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች መተግበሪያውን እንዲዘጉ እንደተነገራቸው ገልጸዋል፡፡

ባለፉት አራት ዓመታት ከ1 ሺህ 600 በላይ ከቲክቶክ ጋር የተያያዙ የሳይበር ደኅንነት ወንጀሎች በኔፓል መመዝገባቸው በሀገራቱ ሚዲያዎች ተዘግቧል።

አሁን ላይ ቲክቶክ ከሳይበር ደኅንነት ጋር ተያይዞ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ከሀገራት የማኅበራዊ ትሥሥር ገፅ ዝርዝር እየታገደ ይገኛል፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version