Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቢሮው ከ33 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ33 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው የሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ሲሆን÷በበጀት ዓመቱ እንደ ከተማ 140 ነጥብ 29 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡

ቢሮው በሩብ ዓመቱ ከ33 ቢሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ የእቅዱን 94 ነጥብ 67 በመቶ ማሳካቱንም የቢሮው ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ አስታውቀዋል።

ግብር ከፋዮች በጊዜ ግብራቸውን አሳውቀው እንዲከፍሉ የተለያዩ የግንዛቤ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ በመድረኩ ተነስቷል።

በዘመን በየነ

Exit mobile version