የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና ሳዑዲ ዘርፈ ብዙ ግንኙነት እንዳላቸው አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ገለጹ

By Amele Demsew

November 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና ሳዑዲ ግንኙነት ባለብዙ ዘርፍ እንደሆነ በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ገለጹ፡፡

አምባሳደር ሌንጮ በሳዑዲ የተካሄደውን የሳዑዲ – አፍሪካ ጉባኤ አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት÷ኢትዮጵያና ሳዑዲ በታሪክ፣በሃይማኖት፣በባህልና ሌሎች ዘርፎች የተሳሰረ መጠነ ሰፊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው ብለዋል፡፡

በተለይም ከለውጡ ወዲህ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ እየጠነከረ መምጣቱን ነው አምባሳደሩ የገለጹት፡፡

በቅርቡ የሳዑዲ መንግስት ወደ ግማሽ ሚሊየን ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የሥራ ስምሪት ፈቃድ መስጠቱ በመልካምነት የሚታይ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

የተሰጠው የሥራና ስምሪት ፈቃድ በሕክምና፣ በኤሌክትሪክ ፣ በግንባታ፣ በሆቴል ማኔጅመንትና በሌሎች ዘርፎች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ሳዑዲ ዓረበያ ለኢትዮጵያ ነዳጅ ለማቅረብና በሌሎች የሃይል ዘርፎች በጋራ ለመስራት ስምምነት መፈረሟንም አስረድተዋል፡፡

ሳዑዲ ኢትዮጵያ ውስጥ መዕዋለ ንዋያቸውን ከሚያፈሱ ሀገራት ውስጥ አንዷ መሆኗን ገልጸው÷በኢትዮጵያ የመሰረተ ልማት ስራዎች ላይም ፋይዳ ያለው ድጋፍ እያደረገች እንደምትገኝ ጠቁመዋል፡፡

በአመለወርቅ ደምሰው

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!