የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ ሒደትን ጎበኙ

By Amele Demsew

November 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት በመዲናዋ እየተሰሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

በዚህም የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ ሒደትን፣ የሴቶች ተሃድሶ እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች÷ፕሮጀክቶቹ በግንባታ ሒደታቸው ለበርካታ ነዋሪዎች የስራ እድል የፈጠሩ በመሆናቸው ትኩረት ሰጥተን ከምንከታተላቸው ስራዎች ውስጥ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ ብለዋል ፡፡

የፕሮጀክቶቹ የግንባታ ሒደት እየተፋጠነ እንደሆነ መገንዘባቸውንም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

አዲስ አበባን ማህበራዊ ፍትሕ የነገሰባት ምቹ የሥራ እና የመኖሪያ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ለማድረግ በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡