የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Amele Demsew

November 10, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አኪንዉሚ አዴሲና ጋር ተወያይተዋል፡፡

በሞሮኮ ማራካሽ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ፎረም ጉበኤ እየተሳተፉ የሚገኙት ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከፕሬዚዳንት አኪንዉሚ አዴሲና ጋር በቀጣይ የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ስርዓት ማሻሻያና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በተጨማሪም በተለያዩ ስትራቴጅክ እቅዶች ላይ መምከራቸውን አስታውቀዋል