የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከጂቡቲ፣ሶማሊያ፣ ታንዛኒያና ሩዋንዳ ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያዩ

By Amele Demsew

November 10, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሳዑዲ – አፍሪካ ጉባኤ ጎን ለጎን ከጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌህ ፣ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼህ ሞሃመድ ፣ከታንዛኒያዋ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉህ ሃሰን እና ከሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፓል ካጋሜ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች እንዲሁም ግንኙነቶችን ስለማጠናከር ላይ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል።