ዓለምአቀፋዊ ዜና

አሜሪካ በዓለማችን የመጀመሪያውን የቺኩንጉንያ ቫይረስ ክትባት አጸደቀች

By Alemayehu Geremew

November 10, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በዓለማችን የመጀመሪያውን የቺኩንጉንያ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል አጸደቀች፡፡

በትንኝ ንክሻ የሚተላለፈው ቫይረስ ክትባት በጤናው ዘርፍ ላይ የሚሠሩት የአሜሪካ ባለሥልጣናት በትናንትናው ዕለት መክረው ማፅደቃቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

“ኢክቺክ” በሚል ሥም ለገበያ የሚቀርበው ክትባት ዕድሜያቸው 18 አመት እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከፍተኛ የመጋለጥ ዕድል ላላቸው ሰዎች የተፈቀደ መሆኑን የአሜሪካ የምግብ እና የመድሐኒት አሥተዳደር አስታውቋል።

የቺኩንጉኒያ በሽታ በኢትዮጵያ ውስጥ ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በተደጋጋሚ እየተከሰተ ጉዳት በማድረስ የሚታወቅ ሲሆን በሽታው በትንኝ ወይም በቢንቢ ንክሻ የሚተላለፍ ነው።