የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ስለሺ ከአሜሪካው ሴናተር ማይክ ሮንድስ ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

November 10, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ኢ/ር) ከአሜሪካው ሴናተር ማይክ ሮንድስጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ባለው የሁለትዮሽ እና ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአፍሪካ የእድገትና ዕድል ድንጋጌ (አጎዋ) ተጠቃሚነት እና ንግድ ዙሪያ መወያየታቸውን አምባሳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አተገባበር እና በሰብዓዊ እርዳታ ሥርጭት ላይ መምከራቸውን አንስተዋል፡፡