Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሳዑዲ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ለሚገኙ የልማት ስራዎች ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከሳዑዲ ዓረቢያ ገንዘብ ሚኒስትር መሃመድ አል ጅዳን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ ልማት እና እዳ ሽግሽግ ላይ መምከራቸውን በሳዑዲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

የሳዑዲ ዓረቢያ ፋይናንስ ሚኒስትር መሃመድ አል ጅዳን÷መንግስታቸው በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ለሚገኙ የልማት እንቅስቃሴዎች በቀጣይነት ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

ውይይቱ በሪያድ እየተካሄደ ከሚገኘው የሳዑዲ ዓረቢያ- አፍሪካ ኢኮኖሚ ኮንፍረንስ ጎን ለጎን ነው የተደረገው፡፡

Exit mobile version