የሀገር ውስጥ ዜና

የሴቶችን አቅም ማጎልበት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ

By Meseret Awoke

November 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግስታት የሴቶች የኢትዮጵያ ተወካይ ሴሲል መኩሩቡጋ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በሥርዓተ ጾታ እኩልነት እና የሴቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በትኩረት መክረዋል፡፡

በተጨማሪም የህጻናት ክብካቤ ተቋማትን ማቋቋም፣ በግጭት እና በድርቅ በተጎዱ ክልሎች የሴቶችን የመቋቋም አቅም መገንባት፣ የተቋማዊ ሥርዓት ግንባታ እና ቅንጅታዊ አሰራር ተግባራዊ ማድረግ ላይ ተወያይተዋል፡፡

ሥርዓተ ጾታን መሠረት ባደረገው ጥቃት በመጪዎቹ 16 ቀናት የጋራ ሃብት ማሰባሰብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

#Ethiopia #UN

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!