Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያና ሳዑዲ በነዳጅና ኢነርጂ መሥኮች በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ በነዳጅና ኢነርጂ መሥኮች በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ሥምምነት ላይ ደረሱ።

የትብብር ሥምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ እና የሳዑዲ አረቢያ ኢነርጂ ሚኒስትር አብዱል አዚዝ ቢን ሰልማን አል ሳዑድ ፈርመውታል፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል የነዳጅ አቅርቦትን ለማስፋት የረጅም ጊዜ የትብብር ማዕቀፍ ሥምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በኢነርጂ፣ በኤሌክትሪክ፣ በኢኖቬሽን፣ በሳይበር ደኅንነትና በሰው ሰራሽ አስተውሎት መሥኮች ሀገራቱ በትብብር ለመሥራት ሥምምነት ላይ መድረሳቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሥምምነቱ የተፈረመው በሪያድ እየተካሄደ በሚገኘው የሳዑዲ-አፍሪካ የኢኮኖሚ ኮንፈረንስ ላይ ነው፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version