Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ሬድዋን ከጠ/ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለኬንያው ፕሬዝዳንት የተላከውን ልዩ መልእክት አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምባሳደርር ሬድዋን ሑሴን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትርና ልዩ መልዕክተኛ፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የተላከውን ልዩ መልእክት ዛሬ በናይሮቢ ተገኝተው አቅርበዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተላከውን ልዩ መልዕክት ከኬንያ በኩል የተቀበሉት የሀገሪቱ ካቢኔ፣ የዳያስፖራና ውጭ ጉዳይ ተቀዳሚ ሚኒስትሩ ሙሳሊያ ሙዳቫዲ ናቸው።

በአምባሳደር ሬድዋን የተመራው የልዑካን ቡድን ከኬንያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ሁለቱ ሀገራት በሚጋሯቸው የሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

Exit mobile version