ቢዝነስ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 10ኛውን የቦይንግ የጭነት አውሮፕላን አስገባ

By Alemayehu Geremew

November 08, 2023

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ 10ኛውን የቦይንግ (Boeing 777-200LR) የጭነት አውሮፕላን ማስገባቱን አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ ያስገባው ዘመናዊ የጭነት አውሮፕላን ባለሁለት ሞተርና ከ100 ቶን በላይ ጭነት የመሽከም አቅም ያለው ነው ተብሏል።

የአየር መንገዱ አውሮፕላኖች የምዝገባ መለያ በ’A’ ፊደል ይጀምር የነበረ ሲሆን የአዲሱ አውሮፕላን ምዝገባ መለያ ግን በB በመጀመር እና ET-BAA የሚል ስያሜን በመያዝ አዲስ የአውሮፕላን ምዝገባ ምዕራፍ መክፈቱንም ነው አየር መንገዱ ያስታወቀው።