Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በለጠ ሞላ( ዶ/ር ) ከኦኤስሲ ዋና ፀሐፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ)የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ( ዶ/ር ) ከደቡባዊ ትብብር ድርጅት (ኦኤስሲ) ዋና ፀሐፊ ሼህ መንሱር ቢን ሙሳላም ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ÷በትምህርት ትራንስፎርሜሽን፣ በዘርፍ ተሻጋሪ ምርምር፣ በሃገር በቀል ቴክኖሎጂ ልማት በኢኖቬሽንና ዲጂታላይዜሽን ዙሪያ በጋራ ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በለጠ ሞላ( ዶ/ር ) በውይይቱ ወቅት÷ ኢትዮጵያ የያዘችው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ትግበራ የተሳለጠ እንዲሆን ከአጋር አካላት ጋር ተባብሮ መስራት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ከትብብር ድርጅቱ ጋራ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

የደቡባዊ ትብብር ድርጅት (ኦኤስሲ) ዋና ፀሐፊ ሼህ መንሱር ቢን ሙሰለም በበኩላቸው÷ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በቴክኒክ ድጋፍ ፣በትምህርት ትራንስፎርሜሽን፣ በዘርፍ ተሻጋሪ ምርምርና መሰል ዘርፎች በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ቀደም ባሉት ጊዜያት የተጀመረውን “የበትረ ሳይንስ” ተሞክሮ እንደገና ለማስጀመርና ለማስፋት በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ መድረሳቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version