አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2012 በጀት ዓመት በ9 ወራት በግብርና ምርቶች ከ600 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሪ መገኘቱን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ ÷ በበጀት ዓመቱ 9 ወራት 690ሺህ840 ቶን ምርት ለውጪ ገበያ በማቅረብ 818 ሚሊየን 611 ሺህ 770 ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 473 ሚሊየን 959 ሺህ 69 ቶን ምርት በመላክ 658 ሚሊየን 200 ሺህ 550 የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል።
በዚህም 255 ሺህ 340 ቶን የቅባት እህሎች በመላክ 339 ሚሊየን 718 ሺህ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ከተላከው 162 ሺህ 782 ቶን ውስጥ 240 ሚሊየን 775 ሺህ 740 ዶላር የተገኘ ሲሆን ÷ ከተላኩት 367 ሺህ 189 ቶን የጥራጥሬ ሰብሎች ውስጥ ደግሞ 231 ሚሊየን 329 ሺህ 070 ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 249 ሺህ 637 ነጥብ 44 ቶን ተልኮ 154 ሚሊየን 663 ሺህ 650 ዶላር እንዲሁም 1 ሺህ 203 ቶን የተፈጥሮ ሙጫና እጣን በመላክ 4 ሚሊየን 164 ሺህ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 977 ነጥብ 15 ቶን ተልኮ 4 ሚሊየን 204ሺህ6መቶ ዶላር ገቢ ተገኝቷል ነው የተባለው።
በተመሳሳይ 46 ሺህ 232 ቶን ጫት በመላክ 240ሚሊየን 406ሺህ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 44 ሺህ 930ነጥብ 26 ቶን ተልኮ 256 ሚሊየን0373ሺህ 10 ዶላር፣ 657 ቶን የብዕርና አገዳ እህሎች በመላክ 618000 የውጪ ምንዛሪ ለማግኘት ታቅዶ 927 ነጥብ 97 ቶን በመላክ 969 ሺህ 310 ዶላር የተገኘ ሲሆን ከባህር ዛፍ 2ሚሊየን 376 ሺህ 7መቶ የውጪ ምንዛሪ ለማግኘት ታቅዶ 1 ሚሊየን 549ሺህ930 ዶላር መገኘቱን ከኢንዱስትሪና ንግድ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።