የሀገር ውስጥ ዜና

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተማሪዎች ውጤት ማሻሻያ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

By Shambel Mihret

November 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2016 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ውጤት ማሻሻያ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

ምክክሩ በዋናነት በ2015 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እና የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዝቅ ማለትን ተከትሎ በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማምጣት በማለም እንደተዘጋጀ ተገልጿል፡፡

በምክክሩ ላይ የተማሪዎችን ውጤት ከማሻሻል ባለፈ ተወዳዳሪና ብቁ ተማሪዎችን ለማፍራት ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ያሉ ትምህርት ቤቶችን ደረጃቸውን የጠበቁ ለማድረግ የሚያስፈልገውን ሀብት አስመልክቶም ትኩረት ተሰጥቶት ውይይት ይደረግበታል ተብሏል።

በምክክሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዞን አስተዳዳሪዎችና የትምህርት ዘርፉ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ነው።

በዓለምሰገድ አሳዬ