DCIM100GOPROGOPR1064.JPG

የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በ42ኛው ዓለም አቀፍ የጉዞ ኢንዱስትሪ ገበያ አውደ ርዕይ ላይ እየተሳተፈች ነው

By Alemayehu Geremew

November 06, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በ42ኛው ዓለም አቀፍ የጉዞ ኢንዱስትሪ ገበያ አውደ ርዕይ ላይ እየተሳተፈች ነው።

42ኛው ዓለም አቀፍ የጉዞ ኢንዱስትሪ ገበያ አውደ ርዕይ በእንግሊዝ ለንደን የኤግዚቪሽን እና የስብሰባ ማዕከል በይፋ ተከፍቷል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ቱሪዝም ሚኒስትር ናሲሴ ጫሊን ጨምሮ በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ተገኝተዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ዓየር መንገድ አቶ ሄኖክን ጨምሮ በኢትዮጵያ የሚሠሩ የተለያዩ የጉዞ ወኪሎች በመርሐ-ግብሩ ላይ መታደማቸውንም በእንግሊዝ የኢትዮፕያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል፡፡

በአሁኑ ሠዓት መርሐ-ግብሩን በርካታ ባለ-ድርሻ አካላት እየታደሙት እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡

በየዓመቱ የሚካሄደው ይህ አውደ ርዕይ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጉዞ ቱሪዝም ዘርፍ ቀዳሚው እንደሆነ ይነገርለታል።