የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ አወል አርባ በገቢ ረሱ ቦሎይታ ቀበሌ የጤፍ ማሳን ጎበኙ

By ዮሐንስ ደርበው

November 04, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በገቢ ረሱ ቦሎይታ ቀበሌ በ200 ሔክታር ላይ እየለማ የሚገኘውን የጤፍ ማሣ ጎብኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የጀመርነውን ጥረት በማጠናከር ታላቅ ሀገር የመገንባት ዕቅዳችንን እውን እናደርጋለን ብለዋል።

በግብርና ዙሪያ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ለአርሶ አደሩ የሚደረገው ድጋፍ ቀጣይነት እንደሚኖረው አረጋግጠዋል፡፡

በተለይም ወንዝ እና ምቹ መሬት የሚገኝበትን አካባቢ በመጠቀም በምግብ እራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት ከግብ ለማድረስ እንደሚሠራም ነው ያመላከቱት፡፡