Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

መጪውን ጊዜ የዋጀ አመራርና የተቋም ግንባታ ዕውን እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ውስጣዊ አቅምን በማጠናከር ተለዋዋጩን ዓለም የዋጀና የውጭ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችል የሪፎርም ሥራ ሕያው ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የአፍሪካ የአመራር ልኅቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት ዛዲግ አብረሃ ገለጹ፡፡

አቶ ዛዲግ “የሪፎርም መሠረታዊያንና የምክር ቤት አባላት ሚና” በሚል ርዕስ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአፍሪካ የአመራር ልኅቀር አካዳሚ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

በሰጡት ስልጠና ላይ ሪፎርሙ የሀገራችንን የፖለቲካ ባሕልና ማኅበራዊ ለውጥ እንዲሁም የሀገር በቀል ዕሳቤዎች መሠረት በማድረግ ጊዜን በመረዳትና በመግራት መጪውን ዘመን የሚዋጅ ነው ብለዋል፡፡

የነገው የኢትዮጵያ ትልቅ የመልማት አቅም ዕውን የሚሆነውም መጪውን ጊዜ በመረዳትና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በተለይ የሰው ሠራሽ አስተውኅሎት ሥራዎችን በማጠናከር በተቋማት ውስጥ በምናደርጋቸው የሪፎርም ሥራዎች መተግበር ይገባል ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ ካለው ዓለም አቀፋዊ ለውጥ አኳያ መሄድ ከቻለች ለውጡ ትልቅ ዕድል እንደሆነ አስረድተው÷ ካልተጠቀመችበት ግን ብዙ ነገር ያሳጣታል ማለታቸውን ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

አዲሱ የዓለም ሀገራት ሁኔታ ለኢትዮጵያ ብልጽግና ጥሩ ዕድል ይዞ እንደሚመጣ ያነሱት አቶ ዛዲግ÷ የ”ብሪክስ” ሀገራት አባል መሆኗ የዚሁ አንዱ ማሳያ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version