Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በ390 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ኤስ ፒ ሲ ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በ390 ሚሊየን ብር ያስገነባውን ሴራሚክን የሚተካ የኤስ ፒ ሲ ፋብሪካ አስመርቋል፡፡

ፋብሪካው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት ለምረቃ በቅቷል፡፡

ፋብሪካው የተገነባው በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር በተቋቋመው በሪሪ ፕሮጀክት ዴቨሎፐር ኃ/የተ/የግ/ማ ነው።

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ጫንጮ ከተማ በ8 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ይህ ፋብሪካ ፥ አሁን ላይ ዓለም የደረሰበትን የመጨረሻውን ቴክኖሎጂ የያዙ ማሽኖች ተገጥመውለታል ተብሏል።

የፋብሪካውን ማሽን ተከላ በ6ወር በማጠናቀቅ ለ130 ዜጎች የስራ እድልን መፍጠሩም ነው የተሰማው።

ፋብሪካው የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ ተረፈ ምርቱን በድጋሚ ስራ ላይ ያውላልም ተብሏል፡፡

በሰዓዳ ጌታቸው፣ ኦሊያድ አህመድ እና ፍቅርተ ከበደ

Exit mobile version