Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጤና አገልግሎቱን ለማሻሻል የሚያስችል አደረጃጀት ተገንብቷል – ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ የጤና አገልግሎቱን ለማሻሻል የሚያስችል አደረጃጀት መገንባቱን የጤና ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ገለጹ፡፡

25ኛው የጤና ዘርፍ ጉባዔ ዛሬ ተጠናቋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ÷ በሀገራችን የጤና የአገልገሎት ማሻሻያ ጥምረት የህዝብ ንቅናቄ ማዕቀፍ በመፍጠር ወደ ትግበራ በፍጥነት ለመግባት የሚስችል አደረጃጀት የተገነባ ነው፡፡

ለዚህም ግንዛቤ መፍጠርና የማስተዋወቅ፣ ግብአቶችን የማቅረብና ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችና ለአገልገሎት ማሻሻያ ጥምረት የቅርብ ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ ለውሳኔ የሚረዳ ወቅታዊ መረጃ የማቅረብ አሰራር በበጀት ዓመቱም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በጉባዔው የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ የተፈረመ ሲሆን ፥ በዚህ ስምምነት የጤና ሚኒስቴር እና የክልል ጤና ቢሮዎች ለ2016 በጀት ዓመት የተቀመጡትን ግቦች ለማሳካት ተስማምተዋል፡፡

በመድረኩ የጤና መረጃ ስርዓት እና የጤና ቴክኖሎጂ ዲጂታይዜሽን ላይ ሊደረጉ ስለሚገባቸው ዝርዝር ተግባራት፣ የጤናው ዘርፍ የሰው ሃብት አስተዳደር አመራር እና የጤና ቁጥጥር ላይ ምክክር መደረጉን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፋርማሲዪቲካልና መድሀኒት አቅርቦት የማህበረሰብ ድንገተኛ የጤና ስጋት ላይ በተለያዩ ቡድኖች ውይይቶች እና ምክክሮችም ተደርጓል።

Exit mobile version