አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራዔል እና ሃማስ ጦርነትት የንጹሐን ደም በከንቱ እንዳይፈስ ተጨባጭ እርምጃ እንዲወሰድ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አሳስበዋል፡፡
ብሊንከን በሚስተዋሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ወደ ቴል-አቪቭ አቅንተዋል፡፡
በዚያም የእስራዔል መሥራች አባት በመባል በክብር የሚታወቁት ዴቪድ ቤን-ጉሪዮን እና ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ 11ኛው የእስራዔል ፕሬዚዳንት የሆኑት አይዛክ ሄርዞግ በጋዜጠኞች እና በካሜራ ታጅበው ተቀብለዋቸዋል፡፡
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ÷ እስራዔል እራሷን ከማናቸውም ጥቃት የመከላከል መብት እንዳላት ገልጸዋል።
“በምን መልኩ እየተከላከለች እንዳለ ግን መጤን አለበት” ብለዋል፡፡
ብሊንከን ከእስራኤል አመራሮችና የጦር መሪዎች ጋር ለአንድ ሰዓት ያኅል ዝግ ሥብሰባ ለማድረግ አቅደው የጀመሩት ውይይት ቀኑን ሙሉ እንዳዋላቸውም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በእስራዔል እና ሃማስ መካከል የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቀረት ቆርጠው እንደተነሱ በዚህ ወቅት ገልጸዋል።
በቀጣይም በጉዳዩ ላይ ለመምከር በመካከለኛው ምሥራቅ የምትገኘውን ዮርዳኖስ እንደሚጎበኙ ተጠቁሟል፡፡
በዛሬው ዕለት ጋዛን ለቀው እንዲወጡ ከተፈቀደላቸው መካከል ወደ 100 የሚጠጉት የብሪታንያ ዜጎች መሆናቸን ዘገባው አመላክቷል።