አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አስተዳደር አልባዘር ቀበሌ ጎዳ በተባለ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሁለት እናቶች እና ሁለት ሕጻናት ልጆቻቸው በአጠቃላይ የአራት ሰው ሕይወት አለፈ፡፡
ዛሬ ከቀኑ 8 ሠዓት ገደማ የደረሰው አደጋ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከወራቤ ወደ ቂልጦ እየተጓዘ ሳለ አካባቢው ላይ ባለው ዳገት በመገልበጡ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በአደጋው ሕይወታቸው ካለፈው አራት ሰዎች መካከል ሁለቱ ሕጻናት ሲሆኑ ሌሎች ሁለቱ ደግሞ የሕጻናቱ እናቶች መሆናውን የወራቤ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ አስተባባሪ ምክትል ሳጅን ቢላል አወል ገልጸዋል።
ሕይወታቸው ካለፈው በተጨማሪም በሌሎች ተሳፋሪዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል ማለታቸውን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ጉዳት የደረሰባቸው ተጓዦችም በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው ነው ብለዋል፡፡
የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑንም ነው ምክትል ሳጅን ቢላል አወል የገለጹት፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!