Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢንፍሉዌንዛ ምንነት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢንፍሉዌንዛ ከጉንፋን ጋር የመመሳሰል ባህሪ ያለው የመተንፈሻ አካላት ህመም ነው፡፡

ምንም እንኳን ጉንፋን እና ኢንፍሎይንዛ አምጪ ቫይረሶች የተለያየ ዓይነት ቢኖራቸውም ህመሞቹ እንደ ማስነጠስ፣ የአፍንጫ ማፈንና ፈሳሽ መብዛት ምልክቶችን የሚጋሩ ናቸው።

የህመሞቹ ምልክት የሚመሳሰሉ ቢሆንም የኢንፍሉዌንዛ ህመም ስሜት ከጉንፋን ከበድ ያለ ነው፡፡

በጣም ከተለመዱት የኢንፍሉዌንዛ ምልክቶች መካከል እንደ ትኩሳት፣ ሳል፣ የጡንቻ ህመም፣ ራስ ምታትና የድካም ስሜት በዋነኝነት ይጠቀሳሉ፡፡

ኢንፍሉዌንዛ ብዙ ጊዜ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሊድን የሚችል የመተንፈሻ አካል ህመም ቢሆንም በደምብ ለመዳን ግን ተጨማሪ ቀናት ሊወስድ እንደሚችል የኸልዝ ላይን መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢንፍሉዌንዛ ህመም ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው ከበልግ ወራት አንስቶ እስከ ጸደይ መጀመሪያ ድረስ እንደሆነም በመረጃው ተካቷል፡፡

በመሆኑም በዚህ ወቅት ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባት በመውሰድ፣ ህዝብ በብዛት በተሰበሰበበት ቦታ ባለመገኘትና ሌሎች የመከላከያ መንገዶችን በመጠቀም የኢንፍሉዌንዛ ተጋላጭነትን መቀነስ እንደሚቻል በመረጃው ተገልጿል፡፡

ኢንፍሉዌንዛ ህመም ከበድ ያሉ ምልክቶች ካሳየ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ የህክምና ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ይህ ካልሆነ ግን ህመሙ ወደ ሳይነስ፣ የጆሮ ህመም፣ ኒሞኒያና መሰል ህመሞች ሊሸጋገር እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

ህክምናውን ቶሎ መጀመር ህመሙ ወደ ሌላ ህመም እንዳይሸጋገር ከማገዙም በላይ የህመሙን ስሜት ለመቀነስም ያግዛል፡፡

በተጨማሪም÷ በኢንፍሉዌንዛ የተያዘ ሰው በቂ እረፍት እንዲያደርግና በቂ ፈሳሽ እንዲወስድ ይመከራል፡፡

በኢንፍሉዌንዛ የተያዘ ሰው በቂ እረፍት እንዲያደርግ ፣ በቂ ፈሳሽ እንዲወስድና እንደ ራስ ምታት እና ትኩሳት ያሉ የህመሙ ምልክቶችን ለመቀነስ የማስታገሻ መድሃኒቶችን ቢወስድ ይመከራል፡፡

ህመሙ ከበድ ያሉ ምልክቶች ካሳየና ቤት ውስጥ በምናደርገው ክትትል ለውጥ ካላመጣ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ የህክምና ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ይህም ህመሙ ወደ ሳይነስ፣ የጆሮ ህመም፣ ኒሞኒያና መሰል ህመሞች እንዳይሸጋገር ያግዛል፡፡

በኢንፍሉዌንዛ የተያዘ ሰው ምልክቶቹን ከማሳየቱ አንድ ቀን በፊት እና ከተያዘ በኋላ ባሉት ከ5 እስከ 7ቀናት ድረስ ወደ ሌላ ሰው ሊያስተላልፍ የሚችልበት አጋጣሚ ሰፊ እንደሆነም መረጃው ያስረዳል፡፡

ስለሆነም ህመሙ ወደ ሌላ ሰው እንዳይዛመት የአፍ መሸፈኛ መጠቀም፣ እጅን በሳሙና መታጠብና ሌሎች የጥንቃቄ መንገዶችን መጠቀም ይመከራል፡፡

Exit mobile version