የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ኩሪፍቱ የአፍሪካ መንደርን ጎበኙ

By Meseret Awoke

November 02, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር እየተገነባ ያለውን የኩሪፍቱ አፍሪካ መንደር ጎብኝተዋል።

አምባሳደሩ ፥ የኩሪፍቱ አፍሪካ መንደር የአህጉሪቱ የፖለቲካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ የአፍሪካን የንግድ ምልክቶች እና እሴቶችን ለማስተዋወቅ ያለውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

የኩሪፍቱ አፍሪካ መንደር ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ባለቤት አቶ ታዲዮስ ጌታቸው ፥ መንደሩ አፍሪካዊ ተልዕኮዎች በመፍጠር የተለያዩ አፍሪካ ሀገራትን ገጽታ በአንድ ቦታ ለማስተዋወቅ ይሰራል ብለዋል።

መንደሩ አፍሪካውያን በታታሪነታቸው አህጉራቸውን በተሻለ ሁኔታ ማስተዋወቅ እንደሚችሉ ማሳያ እንደሆነ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።