Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚዬም ፕሮጀክት ግንባታን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚዬም ፕሮጀክት ግንባታ ሒደት የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡

በግምገማ መድረኩ የተሳተፉት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችም የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚዬም ፕሮጀክት ግንባታ ሒደት የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ የተገኙት የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ደረጃ አስመልክተው ለአመራሩ ገለፃ አድርገዋል።

በዚህም ፕሮጀክቱ የመላው ጥቁር ህዝብ ድል የሆነውን ታላቁን የአድዋ ድል ታሪክ እና የአባቶቻችንን የነፃነት ተጋድሎ እና ጀግንነት በሚመጥን መልኩ በከፍተኛ በጀት እየተገነባ ወደ መጠናቀቁ መቃረቡን ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የከተማ አስተዳደሩን በራስ አቅም ፕሮጀክቶችን የመጀመር፣ የመገንባትና የማጠናቀቅ ብቃት የሚያሳይ ነው ማለታቸውንም የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

አመራሩ በተለያዩ ዘርፎች የተጀመሩና የሕዝቡን የኑሮ ደረጃ በዘላቂነት የሚቀይሩ ዘርፈ ብዙ ፕሮጀክቶችን በዚሁ መንፈስ እንዲመራ እና እንዲያጠናቅቅም አሳስበዋል፡፡

Exit mobile version