Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፖለቲካ ዲፕሎማሲው ስኬት ለኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ሰፊ ዕድል መፍጠሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፖለቲካ መስክ እየተከናወነ ያለውና እየተመዘገበ ያለው የዲፕሎማሲ ስኬት ለኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ሰፊ ዕድል መፍጠሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ በዛሬው እለት መደበኛ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫውን የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም እንዳሉት÷ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ የዲፕሎማሲው ስራ ተሰሚነትን፣ ተጽዕኖ ፈጣሪነትንና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እውን ያደረገበት ነው።

በመሪዎች ደረጃ በተለያዩ ሀገራት የተደረጉ ጉብኝቶች እና ስምምነቶች የቀጥታ ኢንቨስትመንትን ጨምሮ የሀገርን ጥቅም የሚያስጠብቁ የተለያዩ የኢኮኖሚ አማራጮችና ስምምነቶች መከናዎናቸውን አንስተዋል።

በዚህም በሩብ ዓመቱ ከ53 በላይ የውጭ ሀገራት ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የቅድመ ጉብኝት ማድረጋቸው ነው የገለጹት።

ለዚህ ደግሞ በተለያዩ  ሀገራት በተፈጠሩ መድረኮች ኢትዮጵያ ያላት የመልማት አቅም ቀድሞ የማስተዋወቅ ስራ መሰራቱን ጠቅሰዋል።

በሩብ ዓመቱ በቱሪዝም፣ ቴክኖሎጂ እና በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ሰፊ ስራና መነቃቃት መፈጠሩን ጠቅሰው÷ የፖለቲካ ዲፕሎማሲው ስኬት ለዚህ ጉልህ አበርክቶ አለው ብለዋል።

በፍሬህይወት ሰፊው

Exit mobile version