Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሲዳማ ክልል የሕዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዋንጫ ገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

አቶ ደስታ÷ የሕዳሴ ግድብ የማንነታችን መገለጫ፣ የህብረ ብሔራዊነታችንና የአንድነታችን መሰረት ነው ሲሉ አውስተዋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በፊት ለግድቡ የታየው በፅናት መቆም እና አንድነት እሴት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመልክተዋል።

ዞኖች፣ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች በተሰጣቸው እቅድ መሠረት የተጋጋለ ንቅናቄ በመፍጠር እንዲተገብሩም አሳስበዋል፡፡

ተሳታፊዎች ከተሰጣቸው ዕቅድ በተለየ ሁኔታ ለማሳካት በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ መናገራቸውንም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version