አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጋር በመተባበር የማበረታቻ ሽልማቶች እና የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሄደ።
መርሐ-ግብሩ የተካሄደው የሕግ ታራሚዎች በዕውቀት እንዲበለጽጉ እና በሥነ-ምግባር እንዲታነጹ ታሳቢ በማድረግ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
የቤተ-መፅሀፍቱ ዳይሬክተር ኢንጂነር ዉብአየሁ ማሞ እንደገለፁት÷ አሁን ዓለም ከምትገኝበት የሥልጣኔና የዕድገት ደረጃ ልትደርስ የቻለችው በተጻፉና በተነበቡ የዕውቀትና የመረጃ ሥርጭትና ክምችት ሐብቶች የተነሳ ነው።
ንባብ ለአጠቃላይ ስብዕና ዕድገት የሚሰጠው ጠቀሜታ እጅግ ከፍ ያለ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ታራሚዎች ቆይታቸውን ከንባብ ጋር ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበው፤ በማረሚያ ቤት በሚቆይባቸው ዘመናት ጊዜውን የሚያባክንበት ግላዊና ማኅበራዊ ጉዳይ ስለሌለው ከስንፍና፣ ከሞራል ውድቀት፣ ከቀቢጸ-ተስፋ፣ መዳን የሚቻለው በንባብ አማካኝነት ነዉ ማለታቸውን ከቤተ-መፃሕፍቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የማረሚያ ቤት የማረም፣ ማነፅና ተሀድሶ ልማት ዘርፍ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር ጀነራል ደስታ አስመላሽ÷ የአብርሆት ቤተመፃሕፍት ለታራሚዎች ላደረገው ድጋፍ አመስግነው በቀጣይም በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች እንደዚህ ዓይነት ድርጊቶች እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!