Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአዲስ አበባ ከተማና የቹንቾን ከተማ እህትማማችነት 20ኛ ዓመት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማና የደቡብ ኮሪያዋ ቹንቾን ከተማ እህትማማችነት 20ኛ ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ ተከብሯል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣የቹቾን ከተማ ከንቲባ ዮክ ቶንግ ሃን እና የወጣቶች ዲፕሎማሲ ልዑካን ቡድን በተገኙበት የሁለቱ ከተሞች እህትማማችነት 20ኛ ዓመት ተከብሯል፡፡

በተጨማሪም ÷ከንቲባ አዳነችና በዮክ ቶንግ ሃን የተመራው የልዑካን ቡድን የሁለቱ እህትማማች ከተሞች በቀጣይ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ÷በዓሉ መከበሩ ከቹንቾን ከተማ ጋር ለ20 ዓመታት የዘለቀውን የእህትማማችነት ግንኙነት እንደሚያጠናክር ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

የደቡብ ኮሪያዋ ቹንቾን ከተማ አዲስ አበባ ካሏት 24 እህት ከተሞች አንዷ መሆኗን መረጃው አስታውሷል፡፡

Exit mobile version