1 ሚሊየን በላይ ሴቶችና ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

By Melaku Gedif

October 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሄፈር ኢንተርናሽናል ከተሰኘ ድርጅት ጋር በትብብር መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና የሄፈር ኢንተርናሽናል ም/ፕሬዚዳንት አደሱዋ ኢፊዲ ተፈራርመውታል፡፡

ስምምነቱ የእሴት ሰንሰለትን መሰረት ባደረገ የግብርና ሥልጠና የሴቶችንና ወጣቶችን አቅም በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡

በዶሮና እንስሳት እርባታ፣ በወተትና ወተት ተዋጽኦ እንዲሁም በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ከ1ሚሊየን በላይ ሴቶችን እና ወጣቶችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡