የሀገር ውስጥ ዜና

ትምህርት ሚኒስቴር ብቁ መምኅራንን ለማፍራት እየሠራ መሆኑን ገለጸ

By ዮሐንስ ደርበው

October 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ምዘና ሥርዓቱን ለማሻሻል እና ብቁ መምኅራንን ለማፍራት እየሠራ መሆኑን ትምሕርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በጅግጅጋ ከተማ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 36ኛው የመምኅራን ማኅበር ጉባዔ ተጠናቅቋል።

የትምሕርት ሚንስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የትምሕርት ምዘና ሥርዓቱን ለማሻሻል እና ብቁ መምኅራንን ለማፍራት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ብቁ የ2ኛ ደረጃ ትምሕርት ቤቶች ቁጥር ውስን ናቸው ማለታቸውን የሶማሌ ክልል ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡

የክረምት ትምሕርትን በማጠናከር ብቁ መምኅራንን ለመፍጠር የተለያዩ የሞያ ብቃትን የሚያረጋግጡ ስልጠናወችን በመስጠት፣ መምኅራንን በማበረታታት፣ ምቹ የሆኑ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት እና የትምሕርት መሣሪያዎችን ለሟሟላት እየተሠራ እንደሚገኝም አመላክተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!