ቢዝነስ

የሀገር ውስጥ ምርቶች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ሊሠራ እንደሚገባ ተመላከተ

By ዮሐንስ ደርበው

October 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ውስጥ ምርቶችን ጥራት በማረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ተክተው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ሊሠራ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡

የኢንዱሥትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርት ሥትራቴጅ ሠነድ ላይ ከዘርፉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላትና የአምራች ኢንዱሥትሪ ባለቤቶች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

በውይይቱ ላይ÷ የተኪ ምርቶችን የገበያ ድርሻ ከፍ በማድረግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት እንዲቻል የምርቶችን ተወዳዳሪነት አስቻይ ሁኔታን መፍጠር ያስፈልጋል ተብሏል።

የተኪ ምርት ሥትራቴጂው ዓላማም የሀገር ውስጥ አምራቾች ያለውን የገበያ አጋጣሚ በመጠቀም ምርቶቻቸውን በገበያው ተጋሪ እንዲያደርጉ ማስቻል ሲሆን÷ ይህን በማድረግ የውጭ ምርትን በሀገር ውስጥ መተካት የሚቻልበትን ዕድል ማሣደግ እንደሚገባ ተነስቷል፡፡

የተኪ ምርት ሥትራቴጂ የሀገራዊ ማክሮ ኢኮኖሚውን የሚደግፍ መሣሪያ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

ሥትራቴጂክ ሠነዱ ሲዘጋጅም የተኪ ምርት ሂደቱን ሊያጠናክሩ የሚችሉ የማምረት እና የውጭ ምርትን የመተካት ዐቅማቸውን እንዲሁም የዋጋ ተወዳዳሪነት ብሎም የሀገር ውስጥ ግብዓትን ለምርታቸው መጠቀም እና ቴክኖሎጂን ለማዘመን የሄዱበትን ነባራዊ ሁኔታ በመለየት ቅድሚያ እንዲያገኙ ለማስቻል ጥረት መደረጉ ተጠቁሟል፡፡

በይስማው አደራው