Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የክረምት በጎ ፈቃደኞች ከ17 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት አገልግሎት ለሕዝቡ መስጠታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 16 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሳለፍነው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ21 ሚሊየን በላይ ወጣቶች መሳተፋቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

 

የ2015 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ መርሐ ግብር “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ – ሁለት” በሚል መሪ ኃሳብ እየተካሄደ ነው።

 

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አህመድ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፥  በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 21 ሚሊየን 569 ሺህ ወጣቶች ተሳትፈዋል።

 

እነዚህ በጎ ፈቃደኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ በ13 የሥምሪት መስኮች ተሰማርተው ከ17 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት አገልግሎቶች ለሕዝቡ መስጠታቸውንም ነው የገለጹት።

 

በክረምት በጎ ፈቃድ ከተሰጠው አገልግሎት ውስጥ አረንጓዴ አሻራ፣ ደም ልገሳ፣ የማጠናከሪያ ትምህርት፣ የአረጋውያንና የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት ይገኙበታል ብለዋል።

 

በመርኃ ግብሩ የክረምት ወቅት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ ላደረጉ አካላት እውቅና መሰጠቱን ኢዜአ ዘግቧል።

 

Exit mobile version