ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና ከአሜሪካ ጋር የሁለት ወገን አሸናፊነት ላይ የተመሰረተ ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች

By Meseret Awoke

October 25, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከአሜሪካ ጋር የሁለት ወገን አሸናፊነት ላይ የተመሰረተ ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ተናገሩ፡፡

ሺ ለአሜሪካ እና ቻይና ግንኙነት ብሔራዊ ኮሚቴ ዓመታዊ የእራት መርሐ ግብር ተገኝተው፥ ኮሚቴው በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ መስኮች ለሚደረገው ትብብር ያሳየውን የረጅም ጊዜ ትጋት አድንቀዋል፡፡

አክለውም፥ ቻይና ከአሜሪካ ጋር በጋራ ለመስራት እና ለጋራ ብልፅግና ዝግጁ እንደሆነችም ነው የተናገሩት።

ሁለቱ ታላላቅ የዓለም ሀገራት ትክክለኛ የመንግስት ለመንግስት መስተጋብር መንገድ ማግኘት በዓለም ሰላም እና ልማት ላይ እንዲሁም በሰው ልጅ የወደፊት እጣ ፈንታ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመከባበር፣ በሰላም አብሮ የመኖር እና አሸናፊነት የትብብር መርሆዎች ላይ በመመስረት ቻይና ከአሜሪካ ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የሚውል ትብብርን ለማራመድ ዝግጁነቷን ገልጸዋል።

ልዩነቶችን በአግባቡ ለመፍታትና ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የጋራ ጥረቶችን ለማድረግ እንዲሁም ለሀለቱ ሀገራት እንዲሁም ለዓለም ዕድገት የበኩሏን አስተዋፅዖ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኗን ተናግረዋል፡፡

#China #US

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!