የሀገር ውስጥ ዜና

በጅማ፣ ባቱ ፣ ሞጆ እና ሆለታ ከተሞች የተለያዩ የልማት ሥራዎች እየተጎበኙ ነው

By Alemayehu Geremew

October 25, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ፣ ባቱ ፣ ሞጆ እና ሆለታ ከተሞች የተለያዩ የልማት ሥራዎች እየተጎበኙ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች፣ የዶሮ እርባታ፣ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች እንዲሁም የወትተ፣ የከብት ማድለብ እና የንብ ማነብ ሥራዎች እየተጎበኙ ነው፡፡

የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሰል የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በጉብኝቱ ወቅት መገለጹን የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡