Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዓለም የስታርት አፕ ሽልማት ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2023 የዓለም የስታርት አፕ ሽልማት የአፍሪካ ጉባዔ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በአዲስ አበባ  እየተካሄደ ነው።

መድረኩ ኢትዮጵያ በፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ያላትን እምቅ አቅም ለማስተዋወቅ እና በዘርፉ ያላትን ትክክለኛ ገጽታ ለማሳየት የሚያግዝ መሆኑን ከሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ጉባዔው ፈጠራን መሠረት ያደረገ ምጣኔ ሐብት ለመገንባት ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በዚህ ዓመት ከ8 ሺህ 200 በላይ የሚሆኑ ከ54 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ተሳትፈውበታል፡፡

በሥነ ሥርአቱ መጨረሻ ላይ ከመላው አፍሪካ 71 አሸናፊዎች ይሸለማሉ ተብሏል፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version