Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሀገር አቀፍ የጀማሪ ቢዝነሶች ኢንሺየቲቭ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአዳዲስ ሥራና ሀብት ፈጠራ ምቹ ሥነ-ምህዳር ለመፍጠር ያለመ ሀገር አቀፍ የጀማሪ ቢዝነሶች ኢንሼቲቭ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የተለያዩ ሥራ ፈጣሪዎች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

መርሐ ግብሩ በሀገረቀፍ ደረጃ በቴክኖሎጂ ላይ የሚሰማሩና የተሰማሩ አካላት ቅንጅት ፈጥረው ለአዳዲስ ሥራና ሀብት ፈጠራ ምቹ ሥነ-ምህዳር እንዲፈጠርላቸው ለማስቻል ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በመርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልእክት÷ በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ልማትና ፈጠራን ይበልጥ በማጎልበት ለሀገር እድገትና ብልጽግና መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ኢትዮጵያን የበለጸገችና ተጽእኖ ፈጣሪ ለማድረግ የቴክኖሎጂ ልማት ወሳኝ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version